About Us

Our roots trace back to the former Higher 16 Kebele 08, currently known as Woreda 07, in the Congo Veterans Settlement, Afaf Settlement, Asmara Road, and the neighboring settlements in Addis Ababa City, where we were born, raised, and educated. As we matured, reminiscing about our old neighborhood became a topic of conversation during various social events. This led to the creation of a Telegram channel, which attracted a large number of co-developers from both within and outside the country. Through the channel, we were able to exchange information regarding the wellbeing of our elderly parents and neighbors who reside in our old neighborhood. As a result, we decided to initiate a monthly fundraising program to provide financial assistance to those in need. Witnessing this philanthropic gesture, many individuals appreciated and joined in on the effort, including our family members, friends, and relatives. Consequently, we reached a consensus to establish the Congo and Neighborhood Development Association (CNDA) and legally register it with the relevant government body. We firmly believe that this will enable us to expand our outreach and operate lawfully. By doing so, we hope to leave a positive impact on our current and future generations.

Donate now

ዝክረ እኛ

ሥርወ መነሻችን በአዲስአበባ በቀድሞው ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 በአሁኑ ወቅት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 እየተባለ የሚጠራው በኮንጎ የቀድሞ ወታደሮች ሰፈር፣ አፋፍ ሰፈር፣ አስመራ መንገድ አጎራባች ሰፈሮች ተወልደን ያደግንና፣ የተማርን የያኔ ልጆች የአሁን ጎልማሶች በተለያየ ማኅበራዊ አጋጣሚ ስንገናኝ የድሮ ሠፈራችንን በትዝታ በማስታወስ ውይይት እናደርጋለን ። በአጋጣሚ ብቻ ከመገናኘት ለምን ዘመኑ የፈጠረልንን ድህረ ገጽ በመጠቀም አንገናኝም በሚል መነሻ ሀሳብ በሠፈራችን ስም የቴሌግራም ቻናል እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፣ ይህም ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚገኙ አብሮ አደጎች የቻናሉ አባል በመሆን በድሮ ሰፈራችን የሚኖሩ አዛውንት ወላጆቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን ደህንነት በተመለከተ መረጃ መለዋወጥ ችለናል። በዚህም ምክንያት ለተቸገሩት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወርሃዊ የገንዘብ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በመጀመር የበጎ አድራጎት ሥራ ጀምረናል። ይህን እንቅስቃሴያችንን በማየት ቤተሰባችን፣ ጓደኞቻችን እና ዘመዶቻችንን ጨምሮ ብዙ ግለሰቦች ጥረቱን አድንቀው ተካፋይ ሆነዋል። በመሆኑም የኮንጎ ሰፈር እና አካባቢው ልማት ማህበር (CNDA) በማቋቋም ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በማስመዝገብ የእርዳታ ስርጭታችንን በማስፋት መስራት እንደሚያስችለን በማመን የሚከተለውን ዓላማ በማንገብ ወደ ስራ ለመግባት ተነስተናል። ይህን በማድረጋችን የአሁኑ እና ወደፊት ትውልዶቻችን ላይ አወንታዊ ተፅእኖን ማሳረፍ እንችላለን የሚል ተስፋ አለን።

አሁን ይለግሱ
Helping today

What we are doing

Our Association is making a significant impact on the lives of over 40 elderly individuals, encompassing both men and women, who are part of our network. In return, CNDA and its member NGOs are committed to integrating health, food, and inclusiveness initiatives into our shared agenda, advocating for the rights and well-being of elderly individuals.
ማህበራችን የተቸገሩ የሀገር ሽማግሌዎችን ለማንሳት እና ለመደገፍ የጋራ ራዕይና አስተሳሰብ ባላቸው ግለሰቦች ትብብር የሚሰራና በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ለሚገኙ አረጋውያን በምግብ፣ በጤና አጠባበቅ እና በአጠቃላይ ደህንነት ላይ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ የሚጥር ማኅበር ነው።

የበጎ አድራጎታችን ምስክርነት

What They Are Saying About Us

የአብሮ አደግ ማህበራችን በሚያደርገው የበጎአድራጎት መልካም ሥራ በ 2015 ዓ.ም. ተመራጭ ሆኖ፣. በየካ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ለአደረግነው የበጎአድራጎት ሥራ የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል ። አባላቶቻችን  በሀገር ውስጥም በውጭም የምትኖሩ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎ አሁንም  በማህበራችን ስም ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን ።

ማህበራችን በሚያደርገው የበጎአድራጎት መልካም ሥራ በ 2015 ዓ.ም. ተመራጭ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል ። ለዚህ በጎ ሥራ የሁሉም አብሮ አደጎቻችን ተሳትፎና የቴሌግራም ገፅ አባላቶቻችን ተሳትፎ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ። አባላቶቻችን  በሀገር ውስጥም በውጭም የምትኖሩ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎ  በማህበራችን ስም ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን ።

ማኅበራችን በሠፈራችን ለሚገኘው አንጋፋ የሐመረ ኖህ መረዳጃ ዕድር ላደረገው ድጋፍ ከምስጋና ጋር የተሰጠ ሰርተፊኬት ።